በኮልፌ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ የ"ግሪን ቲቬት" ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል
በኮልፌ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ዘላቂነት ያለው፣ ንጹህና ማራኪ የሥራ አካባቢን ለመፍጠር ያለመ የ"ግሪን ቲቬት" የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ለግቢው ማህበረሰብ ተሰጥቷል ።
የኮልፌ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ የተቋማት አቅም ግንባታ ም/ዲን ተወካይ አቶ ሃብታሙ አያንሳ እንደተናገሩት፣ ስልጠናው በዋናነት ትኩረቱን ያደረገው አካባቢን በጋራ ስለማጽዳትና በቆሻሻ አወጋገድ ስርዓት ላይ ሲሆን፣ ተቋሙን ለስራ ምቹና ሳቢ የማድረግ ስራዎችን ለማገዝ ታስቦ መዘጋጀቱን ገልጸዋል ።
በመርሃ ግብሩ ላይ በግሪን ቲቬት መርሃ ግብር የሚበሉና የማይበሉ የጓሮ አትክልቶችን የማልማት ስራ በመጠኑም ቢሆን እየተከናወነ ይገኛል ብለዋል። ይህ እንቅስቃሴ ከመማር ማስተማር ሂደቱ ጎን ለጎን የሚከናወን መሆኑን ጠቁመው፣ ንጹህና ማራኪ ከባቢያዊ ሁኔታን ለመፍጠር ጥረቶች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል።
.