
20ኛውን የብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች በዓልን ምክንያት በማድረግ በኮልፌ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ሰልጣኞች መካከል ወንድማማችነትን የሚያጠናክር የእግር ኳስ ግጥሚያ ተካሂዷል፡፡
በሀገራችን "ዴሞክራሲያዊ መግባባት ለሕብረ ብሔራዊ አንድነት" በሚል መሪ ቃል እየተከበረ የሚገኘውን 20ኛው የብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች በዓልን አስመልክቶ በተዘጋጀው በዚህ ስፖርታዊ መርሃ-ግብር ላይ፤ የኮሌጁ አሰልጣኞች ፣ የአስተዳደር ሰራተኞች እና ሰልጣኞች ተገኝተዋል፡፡
በዓሉን ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀው የእግር ኳስ ጨዋታ፤ በኮሌጁ ሰልጣኞች መካከል ያለውን ወንድማማችነት እና አንድነት ይበልጥ ለማጠናከር ያለመ መሆኑም ተገልጿል፡፡
የብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች በዓል በየዓመቱ ሕዳር 29 ቀን በመላው ኢትዮጵያ በተለያዩ ዝግጅቶች የሚከበር ሲሆን፤ የዘንድሮው የ2018 ዓ.ም በዓልም በኮልፌ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ በድምቀት መከበሩን ለማወቅ ተችሏል፡፡
For all Level one trainers you should submit Trainee Grade report untill the end of this mont
We make sure you have everything you need to succeed as a trainer and edupreneur.
Raise your question