Application Form የ"ወርቃማው ሰኞ" የ6 ወራት የእቅድ አፈጻጸም ግምገማ ተካሂዷል ።

የ"ወርቃማው ሰኞ" የ6 ወራት የእቅድ አፈጻጸም ግምገማ ተካሂዷል ።

12th January, 2026

የ"ወርቃማው ሰኞ" የ6 ወራት የእቅድ አፈጻጸም ግምገማ ተካሂዷል ።

የኮልፌ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ "ወርቃማው ሰኞ" የተሰኘው መርሃ ግብር ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ እስከ ታህሳስ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ የነበረውን የስድስት ወራት የእቅድ አፈጻጸም ክንውን በዛሬዉ ዕለት ባካሄደው መድረክ ገምግሟል።

በግምገማ መድረኩ ላይ የኮሌጁ የኮሙኒኬሽን እና ሕዝብ ግንኙነት ቡድን መሪ አቶ ሰፊው ባንቲሁን ዝርዝር ሪፖርት አቅርበዋል። አቶ ሰፊው በሪፖርታቸው እንደገለጹት፤ የወርቃማው ሰኞ መርሃ ግብር ዋና ራዕይ ጥራቱን የጠበቀና ተደራሽ አገልግሎት ለመስጠት እንዲቻል፣ በሳምንቱ የመጀመሪያ የሥራ ቀን በሠራተኛው ዘንድ ከፍተኛ መነሳሳትንና ሥነ-ልቦናዊ ለውጥን መፍጠር ነው ብለዋል።

ባለፉት ስድስት ወራት የታቀዱ ተግባራትን በዳሰሰው በዚህ ሪፖርት፣ የሚከተሉት ነጥቦች እንደ ትልቅ ስኬት ተጠቅሰዋል፦

 የውስጥ ሠራተኞችን አቅም በመጠቀምና የውጭ እንግዶችን በመጋበዝ፣ መርሃ ግብሩ ሳይቋረጥ እንዲቀጥል መደረጉ።

 ከዚህ ቀደም ይስተዋል ከነበረው "ጥቁር ሰኞ" (የሥራ ድብርት) ስሜት ወደ "ወርቃማው ሰኞ" የሚደረገውን ሥነ-ልቦናዊ ሽግግር በተሳካ ሁኔታ ማስጀመር መቻሉ ተገልጿል።

በዕለቱ እስካሁን በተካሄዱ መርሃ ግብሮች ላይ ዕውቀት በማካፈልና በአቅራቢነት ለተሳተፉ አካላት የዕውቅና ምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል።

የኮሌጁ ዋና ዲን ዶ/ር ቢኒያም አወቀ በመርሃ ግብሩ ማጠቃለያ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ተቋማዊ ለውጥን ተከትሎ መጓዝ ወሳኝ መሆኑን አፅንዖት ሰጥተዋል። 

"ምንጊዜም ቢሆን ለውጥን ተከትሎ መሄድና በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ራስን መሸጥ የሕይወት መርህ ሊሆን ይገባል" ያሉ ሲሆን ፣ ሌሎችም ሠራተኞች በአቅራቢነት በመሳተፍ የድርሻቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።

ይህ መርሃ ግብር በኮሌጁ ውስጥ አዲስ የሥራ ባህልን በመገንባት ረገድ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝም ታውቋል።

.

Copyright © All rights reserved.

Created with