የዘንድሮውን የገና በዓል ምክንያት በማድረግ በኮልፌ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ለዝቅተኛ ደሞዝ ተከፋይ ለሆኑ የኮሌጁ ሠራተኞች የማዕድ ማጋራት መርሐ ግብር ተከናዉኗል።
የቴክኖሎጅ ልማት እና ኢንደስትሪ ኤክስቴንሽን ም/ዲን ወ/ሮ አስናቀች መንግስቱ እንደተናገሩት ይህ የበጎ አድራጎት ተግባር የተከናወነው በዓሉን በጋራና በደስታ ለማሳለፍ እንዲሁም በሠራተኞች መካከል ያለውን መረዳዳትና አንድነት ለማጠናከር ታስቦ መሆኑ ገልፀዋል ።
ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የኮሌጁ ሠራተኞች በዓሉን ያለምንም የኢኮኖሚ ጫና ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንዲያሳልፉ የራሱ አስተዋፅኦ ይኖረዋል ብለዋል።
በመርሐ ግብሩ ላይ በነፍስ ወከፍ የተዘጋጁ ከዘጠና ሺህ ብር በላይ ወጭ የተደረገባቸዉ የዳቦ ዱቄት፣ የምግብ ዘይት ፣ እና ተጨማሪ የገንዘብ ስጦታ ለዝቅተኛ ደሞዝ ተከፋይ ለሆኑ ሰራተኞች የማከፋፈል ሥነ-ሥርዓት ተከናውኗል።
በድጋፉ ተጠቃሚ የሆኑ ሠራተኞች እንደገለጹት፤ እንዲህ ያሉ መርሐ ግብሮች የሠራተኛውን የሥራ ተነሳሽነት ከመጨመር ባለፈ፣ በኮሌጁ ውስጥ የቤተሰባዊነት መንፈስ እንዲሰፍን ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ብለዋል።
ከዚህ ባሻገር ኮሌጁ ላደረገላቸው ድጋፍና ላሳያቸው አጋርነት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
.