Application Form የሴት አሰልጣኞች ፎረም ለመመስረት የሚያስችል የውይይት መድረክ ተካሂዷል

የሴት አሰልጣኞች ፎረም ለመመስረት የሚያስችል የውይይት መድረክ ተካሂዷል

12th January, 2026

የሴት አሰልጣኞች ፎረም ለመመስረት የሚያስችል የውይይት መድረክ ተካሂዷል

​የኮልፌ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ በስራና ክህሎት ሚኒስቴር፣ በቴክኒክና ሙያ ስልጠና ዘርፍ ስር የሚዋቀረውን የሴቶች ፎረም ለመመስረት የሚያስችል የረቂቅ ማስፈፀሚያ ሰነድ ላይ ከሴት አሰልጣኞች ጋር ሰፊ ውይይት አከናወኗል።

​የመድረኩን መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የቴክኖሎጂ ልማት እና ኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ም/ዲን ወይዘሮ አስናቀች መንግስቱ እንደገለጹት፤ ይህ ፎረም መመሥረቱ በሴት አሰልጣኞችና አመራሮች መካከል ጠንካራ ትስስር ለመፍጠር የሚያስችል ነው ብለዋል። 

ከዚህ ባሻገር ​መተጋገዝ እና መደጋገፍ እንዲሰፍን፣ ​የእርስ በርስ መማማር እና መናበብ እንዲዳብር፣ ​በተቋማዊ እንቅስቃሴዎች ላይ የሴቶችን ተሳታፊነት እና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት አስገንዝበዋል።

​የማስፈፀሚያ ሰነዱን ለተሳታፊዎች ያቀረቡት አሰልጣኝ ትዕግስት ዋለልኝ በበኩላቸው፤ ፎረሙ በውስጡ የተለያዩ ተግባራትን የሚያከናውኑ ንዑሳን አደረጃጀቶች እንደሚኖሩት አብራርተዋል።

​በዕለቱም በረቂቅ ሰነዱ ላይ ሰፊ ውይይት ከተደረገ በኋላ፣ ፎረሙን ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ ልዩ ልዩ ኮሚቴዎች ተዋቅረዋል። ይህ አዲስ አደረጃጀት በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ የሚገኙ ሴት ባለሙያዎች ሙያዊ ብቃታቸውን እንዲያሳድጉና በጋራ እንዲሰሩ ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል ተብሎ ይጠበቃል።

.

Copyright © All rights reserved.

Created with