የኮልፌ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ አመራር እና ሰራተኞች በሐገር አቀፍ ደረጃ በመትከል ማንሰራራት በሚል መሪ ቃል እየተከናወነ በሚገኘው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ላይ ከተያዘው እቅድ አኳያ ውጤታማ ተሳትፎ ማድረጋቸውን የኮሌጁ ዲን ገልፀዋል፡፡
የኮሌጁ ዲን ዶክተር ቢኒያም አወቀ እንደገለጹት በአንድ ጀንበር 700 ሚሊየን ችግኝ የመትከል መርሃ ግብር ላይ ባስተላለፉት መልዕክት የኮሌጁ አመራር እና ሰራተኞች ከማለዳው 12 ፡ 00 ሰዓት ጀምሮ በትንሹ አስር ችግኞችን በነፍስ ወከፍ የመትከል እቅድን ለማሳካት ሁሉንም የኮሌጁ ሰራተኞች ባሳተፈ ሁኔታ ዘነብ ወርቅ አካባቢ በተዘጋጀ የችግኝ መትከያ ቦታ ላይ ተሰማርተው በርከት ያሉ ሃገር በቀል ቸግኞችን መተከላቸውን አስታውቀዋል፡፡
.