"ብሩህ አዕምሮዎች በክህሎት የበቁ ዜጎች" በሚል መሪ ቃል በተከበረው 15ኛው ከተማ አቀፍ የቴክኒክ እና ሙያ ሳምንት የቴክኖሎጅ አውደ ርዕይ ውድድር ኮልፌ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ሰባት አይነት ደረጃዎችን በመያዝ ከመቸውም ጊዜ በላይ በላቀ ሁኔታ አስደናቂ ድልን ተጎናጽፏል፡፡
ኮልፌ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ከሰኔ 7 ቀን ጀምሮ ላለፉት አምስት ቀናት ለህዝብ ክፍት ሆኖ በቆየው የቴክኖሎጅ አውደ ርዕይ በአሰልጣኝ ሰልጣኝና እና በኢንተርፕራይዝ የተሰሩ ቴክኖሎጅዎችን ለውደድር ያቀረበ ሲሆን በተገኘው ውጤት
በማምረቻ ዘርፍ አንድ ወርቅ እና አንድ ነሐስ ፤
በምርት ቴክኖሎጅ 3ኛ በመውጣት የነሃሰ ደረጃ ፤
በአይ ሲቲ -የብር፤
በክህሎት ውደድር (በምግብ ዝግጅት) ፤ የነሃስ ደረጃ
በፋሽን ሾው ከ14ቱ ኮሌጆቸ 3ኛ በመውጣት የነሃስ ደረጃ፤
እና በጠረፔዛ ቴኒስ ሁለተኛ በመውጣት የብር ደረጃን በመያዝ በአጠቃላይ በሰባት አይነት ደረጃዎች አሸናፊ ሆኗል፡፡
የኮሌጃችን ዋና ዲን ዶ/ር ቢንያም አወቀ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን የተገኘው ድል የብዙዎች ጥረት ውጤት መሆኑን በማውሳት በጉጉት ስትጠባበቁ ለነበራችሁ የኮሌጃችን ማህበረሰብ በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል፡፡
.