Application Form በ2017 በጀት ዓመት ከታቀዱ ተግባራት ብዙዎቹን በአጠረ ጊዜ ዉስጥ ማሳካት መቻሉ ተጠቆመ።

በ2017 በጀት ዓመት ከታቀዱ ተግባራት ብዙዎቹን በአጠረ ጊዜ ዉስጥ ማሳካት መቻሉ ተጠቆመ።

10th July, 2025

የኮልፌ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ በ2017 በጀት ዓመት የታቀዱ  በርካታ  ተግባራትን ለማከናወን ፣ ለውጥን በጋራ ለማረጋገጥ በግልም በቡድንም ጥረቶች  እንደነበሩና ብዙ ውጣ ውረዶች በማለፍ ስኬቶችን ማስመዝገብ መቻሉን የኮሌጁ  ዋና ዲን በበጀት ዓመቱ የማጠቃለያ ሪፓርት ግምገማ ላይ ተናግረዋል

የኮልፌ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ዋና ዲን ደ/ር ቢንያም አወቀ እንዳብራሩት በተለይም  በዘንድሮው የቴክኒክና ሙያ ሳምንት በተካሄደው የቴክኖሎጅ ውድድር ላይ የተገኘው ውጤት እና ለስልጠና ምቹ ከባቢያዊ ሁኔታ ለመፍጠር እየተሰሩ ያሉ የመሰረተ ልማት ስራዎችን ለአብነት ጠቅሰዋል፡፡ 

ከዚህ በተጨማሪ ኮሌጁ ወደ ምርት ለመሰማራት በስምንት የሙያ ዘርፎች ኢንተርፕራይዝ ማቋቋሙና  ስራ መጀመር በሚያስችል ዝግጅት ላይ መደረሱ እና  ሌሎች በሰራተኛው እና በባለድርሻ አካላት መካከል ሲነሱ የቆዩ  የመልካም አስተዳደር ችግሮች እና የተፈቱበት አግባብን  ዘርዝረው ውጤታማነት የተንጸባረቀበት በጀት ዓመት ነበር ብለዋል፡፡  

የስልጠናና አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ዲን ወ/ሮ ሳራ አበባ የኮሌጁን የተጠቃለለ ሪፖርት በንባብ ያቀረቡ ሲሆን  ከእነዚህም መካከል የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ምዘናና ከማረጋገጥ ፣ አካል ጉዳተኞችን እና ሴቶች የስልጠና ተጠቃሚ ከማድረግ፣ የአሰልጣኞችን የሙያ ብቃት ከማሳደግ ፣ የማስልጠኛ ተቋማትን ለስልጠና ምቹና ሳቢ ከማድረግ፣ በራስ አቅም ገቢ የመሸፈን አቅምን ከማሳደግ አኳያ ፣ አዋጭ ቴክኖሎጂዎችን ከማሸጋገር አንጻር እና በመሳሰሉ ተግባራት ላይ የተገኙ ውጤቶችን አንስተዋል፡፡

በተጠቃለለው የ2017 በጀት ዓመት  ሪፖርት ላይ  አስተያየት ከሰጡት ባለድርሻ አካላት መካከል አቶ አንተነህ ይርሳው የወረዳ 01 የስራ ዕድል ፈጠራ ባለሙያ  ሲሆኑ በተጀመሩ የመሰረተ ልማት ስራዎች መደመማቸውን ገልጸው  እና  ከ11 ወረዳዎች የተውጣጡ  ከ34 ሺ በላይ ስራ አጥ ወጣቶች በክፍለ ከተማው ብቸኛ በሆነው በዚህ ኮሌጅ ሰልጥነው የስራ እድል ሊፈጠርላቸው ችሏል ብለዋል፡፡

 ይህ ከፍተኛ አሃዝ ሊመዘገብ የቻለው ከባለድርሻ አካላት ጋር ተናቦ የመስራት ቁርጠኝነት ስላለ እና  የኮሌጁን አላማ ለማስፈጸም የቆሙ አሰልጣኞች በመኖራቸው ጭምር የተመዘገበ ነው ብለዋል፡

.

Copyright © All rights reserved.

Created with