Application Form በሪፎርሙ ለተመደቡ አዳዲስ አሰልጣኞች የአቀባበልና የስራ ትውውቅ መድረክ ተካሂዷል።

በሪፎርሙ ለተመደቡ አዳዲስ አሰልጣኞች የአቀባበልና የስራ ትውውቅ መድረክ ተካሂዷል።

12th January, 2026

የኮልፌ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ የተቋሙን ሪፎርም ተከትሎ በቅርቡ ወደ ኮሌጁ ለተቀላቀሉ አዳዲስ አሰልጣኞች የአቀባበልና የስራ ትውውቅ መርሀ ግብር ተካሄዷል።

 በመድረኩም አሰልጣኞች ያላቸውን ልምድና እውቀት በማቀናጀት ለላቀ ውጤት እንዲተጉ የስራ አቅጣጫ ተሰጥቷል።

የኮሌጁ አመራር እንዳስታወቀው፣ ይህ የትውውቅ መድረክ ዋና ዓላማ አሰልጣኞቹ ወደ ስራ ሲገቡ በተሻለ ተነሳሽነት እንዲሰሩ ለማስቻልና ኮሌጁም ለአሰልጣኞች ምቹ የስራ አካባቢን ለመፍጠር ያለውን ቁርጠኝነት ለማሳየት ነው።

በመርሀ ግብሩ ላይ የተገኙት የኮልፌ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ዋና ዲን ዶ/ር ቢንያም አወቀ፤ በቀጣይ የኮሌጁን ተልዕኮ ለማሳካት መከናወን ስላለባቸው ቁልፍ ተግባራት ላይ ገለጻ በመስጠት በስልጠና ጥራት፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር እና ኢንተርፕራይዞችን በመደገፍ ረገድ የሚጠበቀውን ውጤት ለማምጣት ጠንካራ ስራ መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።

ከተለመደው የመማር ማስተማር ሂደት ባሻገር ሁሉም አሰልጣኝ በጥናትና ምርምር ስራዎች ላይ መሰማራት ግዴታ መሆኑን አሳስበዋል። "የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ በተፈጥሮው የቡድን ስራን የሚጠይቅ ነው፤ በመሆኑም በየጊዜው የሚገጥሙንን ክፍተቶች ለመሙላትና ተወዳዳሪ ለመሆን የሁላችንንም ርብርብ ይጠይቃል" ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

በመድረኩ የተሳተፉት አዲሶቹ አሰልጣኞች በበኩላቸው፤ ራሳቸውን ከማስተዋወቅ ባሻገር ቀደም ሲል በነበሩበት የስራ መስክ ያበረከቱትን አስተዋጽኦና ያካበቱትን ልምድ በተመለከተ አጠር ያለ ማብራሪያ በመስጠት በቀጣይም ልምዳቸውን ለኮሌጁ እድገት ለማዋል ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

በውይይቱ ማጠቃለያ ላይ ዶ/ር ቢንያም አወቀ፤ አሰልጣኞች የስራ ሰዓትን በአግባቡ በማክበር፣ ስራን በትኩረት በመስራት እና ተልዕኮዎችን በአንድ ዓላማና በቡድን መንፈስ በመፈጸም የሚጠበቅባቸውን ሙያዊ ኃላፊነት እንዲወጡ አቅጣጫ በመስጠት መድረኩ ተጠናቋል።

.

Copyright © All rights reserved.

Created with