Application Form "ሴቶችን ማብቃት ለሀገር ዕድገት" በሚል መነሻ ሃሳብ ላይ ስልጠና ተሰጥቷል

"ሴቶችን ማብቃት ለሀገር ዕድገት" በሚል መነሻ ሃሳብ ላይ ስልጠና ተሰጥቷል

12th January, 2026

 "ሴቶችን ማብቃት ለሀገር ዕድገት" በሚል መነሻ ሃሳብ ላይ ስልጠና ተሰጥቷል 

በኮልፌ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ በተካሄደው "የወርቃማው ሰኞ" መርሐ ግብር፣ ሴቶችን ማብቃት በሀገር ዕድገት ላይ ባለው ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ዙሪያ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል።

በዕለቱ ስልጠናውን ያቀረቡት ወ/ሮ ትዕግስት ዋለልኝ ሲሆኑ ሴቶችን ማብቃት ማለት ሴቶች የራሳቸውን ምርጫ እንዲያደርጉ፣ ህይወታቸውን እንዲቆጣጠሩ እና የሚኖሩበትን ማህበረሰብ እንዲቀርጹ የሚያስችል ሀይል፣ ሀብት እና እምነት የመስጠት ሂደት እንደሆነ አስገንዝበዋል።

 በማከልም የማብቃት ሂደቱ ዋና ዋና ግቦች የሚከተሉት መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡

ሴቶች ግላዊ ዕድሎችን እንዲያሳኩ ማስቻል፤

ሙሉ አቅማቸውን እንዲያዳብሩ ምቹ ሁኔታን መፍጠር፤

ከማንነታዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ እና ማህበራዊ መሰናክሎች ነፃ እንዲሆኑ ማገዝ ናቸው ብለዋል።

ወ/ሮ ትዕግስት እንዳሉት ሴቶችን ማብቃት የአንድ ወገን ስራ ብቻ አለመሆኑን በማሳሰብ ውጤት ሊመጣ የሚችለው የሴቶች ቁርጠኝነት፣ የወንዶች አጋርነት፣ የማህበረሰቡ የአስተሳሰብ ለውጥ እና የመንግስት ፖሊሲዎች በጋራ ተቀናጅተው ሲሰሩ መሆኑን አስምረውበታል።

የኮሌጁ ዋና ዲን ዶ/ር ቢንያም አወቀ በበኩላቸው፣ ሴቶችን የማብቃት ሚና የሁሉንም አካላት ርብርብ የሚጠይቅ መሆኑን አጽንዖት በመስጠት ኮሌጁ ይህንን ዓላማ ከግብ ለማድረስ በተለየ ሁኔታ የሴቶች ፎረም እንቅስቃሴን በማጠናከር የበኩሉን ድርሻ እንደሚወጣ አረጋግጠዋል።

.

Copyright © All rights reserved.

Created with