
የኮልፌ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ዘወትር ሰኞ ማለዳ የሚያካሄደው የወርቃማው ሰኞ መርሀ ግብር ፕሮግራሙን የኮሌጁ አመራርና ሰራተኞች በተገኙበት አካሂዷል፡፡
የእውቀት ሽግግር እና የህይወት ልምዳቸውን ያካፈሉት የኮልፌ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ አሰልጣኝ የሆኑት አቶ ሲሳይ መኮንን በአንድ የጆን ማክስዌል መጽሐፍ ዙሪያ የእውቀት ሽግግራቸውን አካፍለዋል፡፡
የኮሌጃችን የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ አሰልጣኝ የሆኑት አቶ ሲሳይ መኮንን ሀያ አንዱ የማይለወጡ ሕጎች በሚል ጆን ማክስዌል የጻፈውን መጽሐፍ ተንተርሰው ሀያ አንዱንም ሕጎች በማቅረብ አብራርተዋል፡፡
ጆን ማክስዌል በአመራር ላይ ከዓለም ቀዳሚ ባለሥልጣናት አንዱ እንደሆነ እና ከ ሀምሳ በላይ መጽሐፍቶችን እንደጻፈ ገልጸው ከመጽሐፍቶቹ መካከልም ይህን ሀያ አንዱ የማይሻሩ ሕጎች በሚል ያዘጋጀው መጽሐፍ ሕጎቹን ዘርዝረዋል፡፡ ከሕጎቹ መካከልም የመጀመሪያው የክዳኑ ሕግ የተሰኘው አመለካከት፣ እቅድ እና ስትራቴጂ፣ ተልዕኮ እና አላማ ላይ የሚያተኩር ሲሆን ፤ ሌላኛው የተጽእኖ ሕግ ደግሞ ውጤት ለማምጣት ትልቅ አቅም እንዳለው እንዲሁም የሒደቱ ሕግ ፣ የአሰሳ ሕግ ፣ የመደመር ሕግ ፣ የአክብሮት ሕግ ፣ የማብቃት ሕግ ፣ የመግዛት ሕግ ከሕጎቹ መካከል እንደሚገኙ ጠቅሰው በመጽሐፉ ዙሪያ የተዘጋጁበትን አቅርበዋል፡፡
የኮሌጁ ሰልጣኝ ልማት እና አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ዲን ወ/ሮ ሳራ አበበ በማጠቃለያቸው አቅራቢውን በማመስገን የአሜሪካ ጸሀፊ የሆነውን ጆን ማክስዌልን ጠቅሰው ሕጎቹ በትክክልም ለአመራር ጠቃሚ እንደሆኑ እና ሕጎቹን በማስታወስ ሁሉም ሰራተኛ ለውጤት መስራት እንዳለበት ተናግረዋል፡፡
.