ከመልካም አስተዳደር እና ከአገልግሎት አሰጣጥ በማህበረሰቡ የሚነሱ ጉድለቶችን ነቅሶ በማውጣት የውስጥና የውጭ ተገልጋዮችን ፍላጎት በ2018 በጀት ዓመት ለማሟላት በአመራርና ሰራተኞች መካከል በተዘጋጀ የእንጠያየቅ የውይይት መድረክ በርካታ ችግሮችን በጋራ ለመፍታት ጥረት እንደሚደረግ የኮሌጁ ዲን ገልጸዋል፡፡
የኮልፌ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ዋና ዲን ዶ/ር ቢንያም አወቀ የሰራተኛው ፣ የሰልጣኙ እና የባለድርሻ አካላት ፍላጎት በተንሸራሸረበት የውይይት መድረክ በ2018 በጀት ዓመት የሚከናወኑ ጉዳዮች እና ከእያንዳንዱ ሰራተኛ የሚጠበቀውን ሃላፊነት በመዘርዘር የጀመርነውን የስራ ዘመን የአመራር ግልጸኝነት ፈጥረን ለተግባሮቻችን ትኩረት ሰጥተን ተጨባጭ ለውጥ ለማምጣት እንሰራለን ብለዋል፡፡
በውይይት መድረክ ላይ በ2018 በጀት ዓመት እቅድ ውስጥ ተካተው መፍትሄ እንዲሰጥባቸው በሰራተኛው ከተሰነዘሩ ሀሳቦች ውስጥ የካፍቴሪያ አገልግሎት ማስቀጠል፣ የህንጻ እድሳት ጉዳይ፣ የህጻናት እንክባካቤና ማቆያ ማዕከልን መደገፍ ፣ የውሃ አቅርቦት ችግርን መፍታት፣ የጥገና እና የማከማቻ ክፍሎች እጥረትን መቅረፍ የመሳሰሉ ጉዳዮች ይገኙበታል፡፡
በማጠቃለያ መርሐ ግብሩ ላይ የኮሌጁ ዋና ዲን ሰራተኞች ያነሷቸው በርካታ ሃሳቦች አጽንዖት ሰጥተው እንደሚመለከቱት በመግለጽ በ2018 በጀት ዓመት ትኩረት የሚፈልጉ እና የሚተገበሩ ጉዳዮችን ጠቁመዋል፡፡ የአሰልጣኞች ማረፊያ፣ የሰልጣኝ ካፌ እና ቤተ መጻህፍት ፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማዘወተሪያ ቦታዎችን ማመቻቸት፣ የከርሰ ምድር ውሃ ማሟላት እና የተነሱ ሃሳቦችን ወስዶ ለመተግበር እና አሰልጣኙ የሚጠበቁበትን ጉዳዮች በማንሳት የጋራ ቁርጠኝነት ያስፈልገናል በማለት ያቀድነውን የምናሳካበት ዓመት ይሆናል ብዮ አስባለሁ ብለዋል፡፡
.