የኮልፌ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ አመራሮችና ሰራተኞች በክረምቱ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር የተከሏቸውን ችግኞች የመንከባከብና የክትትል ስራን በዛሬው ዕለት በጋራ አከናዉነዋል።
የኮሌጁ ዋና ዲን ዶ/ር ቢንያም አወቀ፤ የአረንጓዴ ልማት ሥራን ውጤታማ ለማድረግ ከመትከል ወደ ማጽደቅ ግብ መሸጋገር አስፈላጊነት ገልፀዉ የዛሬው ተግባር ኮሌጁ ለሀገራዊዉ የአረንጓዴ ልማት ራዕይ ስኬት ያለውን ጽኑ ቁርጠኝነት የሚያሳይ መሆኑን አስገንዝበዋል።
የተቋማት አቅም ግንባታ ም/ዲን ተወካይ አቶ ሃብታሙ አያንሳ እንደገለፁት የእንክብካቤ ስራዉ በዋነኝነት ያተኮረው በሐምሌ እና ነሐሴ ወር የተተከሉ ችግኞችን በመኮትኮት፣ አረም በማጽዳትና የችግኞቹን ጤናማ ዕድገት በማረጋገጥ ላይ ነው ብለዋል።
በመቀጠል ዋና ዲኑ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብርን ለመደገፍ የከብቶችን ፍግ ወደ ተፈጥሮ ማዳበሪያ በመጠቀም ለአካባቢው ማህበረሰብ አርአያ የሚሆን ተግባር ለማከናወን ስራዎች እየተሰሩ ስለመሆናቸዉ ጠቁመዋል።
በእንክብካቤ ስራው ላይ የተሳተፉት የአመራር አባላትና ሰራተኞች በበኩላቸው የጀመሩት የልማት አሻራ ፍሬ አፍርቶ እንዲታይና ለሀገራዊ የአየር ንብረት ጥበቃ ስራው የበኩላቸውን ድርሻ ማበርከታቸውን እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል።
.