ታህሣሥ 6 ቀን 2018 ዓ.ም
በምግብ አያያዝ እና አበሳሰል ዘዴዎች ላይ ስልጠና ተሰጥቷል
በኮልፌ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ በተካሄደው ሳምንታዊ 'የወርቃማው ሰኞ' መርሐ ግብር ላይ፣ የኮሌጁ የሆቴል እና ሆስፒታሊቲ አሰልጣኝ የሆኑት አቶ ጌታሁን ውድነህ የምግብ አያያዝ እና የአበሳሰል ጥበቦች ዙሪያ አጭር እና ጠቃሚ ሥልጠና ሰጥተዋል።
ሥልጠናው በዋነኛነት የምግብ አያያዝ እና አበሳሰል ዘዴዎች በሚል ርዕስ የቀረበ ሲሆን አቶ ጌታሁን ዉድነህ በመርሐ ግብሩ ላይ ባደረጉት ገለጻ፣ ምግብን ለጤናማነት ከብክለት ነጻ አድርጎ ማዘጋጀት እና መመገብ የሚቻልባቸዉን ሁኔታዎች ሙያዊ በሆነ መንገድ ግንዛቤ ሰጥተዋል።
የኮልፌ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ የቴክኖሎጅ ልማት እና ኢንደስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ም/ ዲን ወ/ሮ አስናቀች መንግስቱ እንደገለፁት ምግብ ቅንጦት ሳይሆን መሠረታዊ ጉዳይ በመሆኑ በምግብ አያያዝ እና አበሳሰል ስርዓታችን ላይ ያሉብንን ክፍተቶች ለመሙላት የተደረገዉን ሙያዊ ገለፃ በተለይም ምግብ ጣዕሙን፣ ንጥረ ነገር እና ጥራቱን ሳይቀየር የተዋጣለት ምግብ ለማብሰል የሚያስችሉ ዘመናዊ እና ባህላዊ ዘዴዎችን ተጠቅሞ ለመገልገል የቀረበዉ ማብራሪያ የሚበረታታ ነዉ ብለዋል።
